ኦ እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ አቡነ ሣህለ ሥላሴ
የመጻሕፍተ ሐዲሳት፣ የመጻሕፍተ ሊቃውንትና የአቡሻኽር መምህር
(ከ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. እስከ ፳፻፰ ዓ.ም.) በቀሲስ ሰሎሞን ወንድሙ መታፈሪያ
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ሐምሌ ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. በዛሬው ምሥራቅ ሸዋ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በጎሎ ሊበን አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ደስአለኝ ኀይሌ እንዲኹም ከእናታቸው ከወ/ሮ ሙላቷ ገብረ ጻድቅ ተወለዱ፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደሳለኝ ስለ ትውልድ መንደራቸው ስለ ቤተሰባቸው ማንነት ሲጠየቁ መልሳቸው “እናቴ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፤ አባቴም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” የሚል ነበር፡፡
የመጻሕፍተ ሐዲሳት፣ የመጻሕፍተ ሊቃውንትና የአቡሻኽር መምህር
(ከ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. እስከ ፳፻፰ ዓ.ም.) በቀሲስ ሰሎሞን ወንድሙ መታፈሪያ
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ሐምሌ ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. በዛሬው ምሥራቅ ሸዋ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በጎሎ ሊበን አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ደስአለኝ ኀይሌ እንዲኹም ከእናታቸው ከወ/ሮ ሙላቷ ገብረ ጻድቅ ተወለዱ፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደሳለኝ ስለ ትውልድ መንደራቸው ስለ ቤተሰባቸው ማንነት ሲጠየቁ መልሳቸው “እናቴ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፤ አባቴም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” የሚል ነበር፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ትምህርት የጀመሩት በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከየኔታ ወልደ ሥላሴ ዘንድ ነበር፡፡ በዝቋላ ከመምህራቸው ዘንድ ንባብና መዝገበ ቅዳሴን ተምረዋል፡፡ በዐሥር ዓመት ዕድሜያቸው በ፲፱፻፴፭ ዓ.ም. ከግብጻዊዉ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ መዐርገ ዲቁና ተቀብለዋል፡፡ በምነና እንዲኹም በሊቅነታቸው ታዋቂ የነበሩት መምህራቸው የኔታ ወልደ ሥላሴ “ይኽ ልጅ እንደ እኔ ይኾናል” ብለው ትንቢትን ተናግረውላቸው ነበር፡፡
ከዝቋላ ገዳም ከተመለሱ በኋላ በደብረ ዘይት ከተማ ዘመናዊ ትምህርት ቤት በመግባት ለኹለት ዓመታት የእንግሊዘኛ ቋንቋን ተምረዋል፡፡ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፵፫ ዓ. ም. በእንጦጦ መንበረ ፀሓይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍተ ሐዲሳትና መጻሕፍተ ሊቃውንት ያስተምሩ ወደነበሩት ስመ ጥሩው መምህር ዘሪሁን ኀሩይ ዘንድ የመምህራቸውን ደብዳቤ ይዘው ትርጓሜ መጻሕፍትን ለመማር ሄዱ፡፡ ከየኔታ ዘሪሁን ዘንድ የቅኔ ትምህርትን በመዠመር ቅኔ ተቀኙ፡፡ በመቀጠልም ከ፲፱፻፵፬ እስከ ፲፱፻፶፩ ዓ. ም. መጻሕፍተ ሐዲሳትንና መጻሕፍተ ሊቃውንትን አኺደዋል፡፡
ይኽ ዘመን በሕይወታቸው ነገረ ሃይማኖትን በጥልቀት ለማጥናት፤ ልቡናቸውን በምሥጢር ለመሙላት እንዲኹም ሕይወታቸውን በቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ ለመምራት የወሰኑበትን አጋጣሚ አመቻችቷል፡፡ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስ አለኝ አስቀድመው ዐሥራ ዐራቱን የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታትን ሙሉ ንባብና ትርጓሜውን በእጃቸው ጽፈው አጠናቀዋል፤ በመቀጠልም ግብረ ሐዋርያትንና የዐራቱ ወንጌላት ትርጓሜን ጽፈዋል፡፡ በተጨማሪም የውዳሴ ማርያምንና የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜን ጽፈዋል፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ከየኔታ ገብረ ወልድ ዘንድ የቀጸሉት ሃይማኖተ አበው ወደ ፊት ጉባኤው እንዳይታጠፍ ከ፲፱፻፶፫ አስከ ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ባሉት ዓመታት የሃይማኖተ አበው ሙሉ ትርጓሜን ከባሕረ ሐሳብ ጋር ጽፈዋል፡፡
በ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. የሊቁ የየኔታ አፈወርቅ የቅኔ አገባብና፣ ዕርባ ቅምሩን፤ የየኔታ ባሕርይ አገባብ የሚባለውን፤ ከዚያም የየኔታ ጌቴ ገሞራ አዋጅ የሚባለውን የቅኔ መንገድ ጽፈዋል፡፡ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከየኔታ ወልደ ሥላሴ የተማሩት ቅዳሴ “ሰለልኩላ” የሚባለውን ስለነበር፤ የደብረ ዐባይን ወዝ ለመያዝ ከየኔታ መዝሙር ንጋቱ “መዝገብ ቅዳሴን” በሚገባ በማጥናት የቅዳሴውን አንቀጽ ከነምልክቱን ጽፈዋል፡፡ በተጨማሪም በእንጦጦ መንበረ ፀሓይ ቅድስት ማርያም ከነበሩት አባቶች ያገኙትን ምዕዳን ጽፈው አስቀምጠዋል፡፡
ይኽ ዘመን በሕይወታቸው ነገረ ሃይማኖትን በጥልቀት ለማጥናት፤ ልቡናቸውን በምሥጢር ለመሙላት እንዲኹም ሕይወታቸውን በቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ ለመምራት የወሰኑበትን አጋጣሚ አመቻችቷል፡፡ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስ አለኝ አስቀድመው ዐሥራ ዐራቱን የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታትን ሙሉ ንባብና ትርጓሜውን በእጃቸው ጽፈው አጠናቀዋል፤ በመቀጠልም ግብረ ሐዋርያትንና የዐራቱ ወንጌላት ትርጓሜን ጽፈዋል፡፡ በተጨማሪም የውዳሴ ማርያምንና የቅዳሴ ማርያም ትርጓሜን ጽፈዋል፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ከየኔታ ገብረ ወልድ ዘንድ የቀጸሉት ሃይማኖተ አበው ወደ ፊት ጉባኤው እንዳይታጠፍ ከ፲፱፻፶፫ አስከ ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ባሉት ዓመታት የሃይማኖተ አበው ሙሉ ትርጓሜን ከባሕረ ሐሳብ ጋር ጽፈዋል፡፡
በ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. የሊቁ የየኔታ አፈወርቅ የቅኔ አገባብና፣ ዕርባ ቅምሩን፤ የየኔታ ባሕርይ አገባብ የሚባለውን፤ ከዚያም የየኔታ ጌቴ ገሞራ አዋጅ የሚባለውን የቅኔ መንገድ ጽፈዋል፡፡ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከየኔታ ወልደ ሥላሴ የተማሩት ቅዳሴ “ሰለልኩላ” የሚባለውን ስለነበር፤ የደብረ ዐባይን ወዝ ለመያዝ ከየኔታ መዝሙር ንጋቱ “መዝገብ ቅዳሴን” በሚገባ በማጥናት የቅዳሴውን አንቀጽ ከነምልክቱን ጽፈዋል፡፡ በተጨማሪም በእንጦጦ መንበረ ፀሓይ ቅድስት ማርያም ከነበሩት አባቶች ያገኙትን ምዕዳን ጽፈው አስቀምጠዋል፡፡
በ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. የሊቁ የየኔታ አፈወርቅ የቅኔ አገባብና፣ ዕርባ ቅምሩን፤ የየኔታ ባሕርይ አገባብ የሚባለውን፤ ከዚያም የየኔታ ጌቴ ገሞራ አዋጅ የሚባለውን የቅኔ መንገድ ጽፈዋል፡፡ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከየኔታ ወልደ ሥላሴ የተማሩት ቅዳሴ “ሰለልኩላ” የሚባለውን ስለነበር፤ የደብረ ዐባይን ወዝ ለመያዝ ከየኔታ መዝሙር ንጋቱ “መዝገብ ቅዳሴን” በሚገባ በማጥናት የቅዳሴውን አንቀጽ ከነምልክቱን ጽፈዋል፡፡ በተጨማሪም በእንጦጦ መንበረ ፀሓይ ቅድስት ማርያም ከነበሩት አባቶች ያገኙትን ምዕዳን ጽፈው አስቀምጠዋል፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ቤተሰቦቻቸው ሀብታቸውን እንዲወርሱ ሚስት እንዲያገቡ ቢመክሯቸው የክርስቶስ ፍቅር አሸንፏቸው ጣዕመ ዓለምን ንቀው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመኼድ መዓርገ ምንኲስናን ተቀብለዋል፡፡ በጠላት ጊዜ ደግሞ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከአቡነ ጎርጎርዮስ ቀዳማይ መዐርገ ቅስናን ተቀብለዋል፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ከቤተሰብ ተለይተውና ከዘመድ አዝማድ ርቀው በምናኔና በጉባኤ ቤት ለበርካታ ዓመታት የኖሩ ታላቅ አባት ነበሩ፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በምንኲስና ሕይወታቸውና በሊቅነት ብቃታቸው የታወቁ በመኾናቸው በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ መልአከ ፀሓይ ተብለው ተሠይመው በተማሩበትና በአደጉበት በእንጦጦ መንበረ ፀሓይ ማርያም አስተዳዳሪነት ተሹመው ለዐምስት ዓመታት ከ፲፱፻፷ ዓ.ም. እስከ ፲፱፻፷፭ ዓ.ም. በእልቅና አገልግለዋል፡፡ ከዚያም፡
፩. በመርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል (ለተወሰኑ ወራት)፤
፪. በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና በጎላ ቅዱስ ሚካኤል (ለኹለት ዓመታት)፤
፫. በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል (ለኹለት ዓመታት)፤
፬. በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም (ለኹለት ዓመት ከመንፈቅ)
፭.በጎፋ መካነ ሕያዋን ኪዳነ ምሕረት (ለዐምስት ዓመት)
፮ በምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ገዳም (ለተወሰኑ ወራት)
፯.በደብረ ገሊላ አማኑኤል በአስተዳዳሪነት አገልግለዋል፡፡
፰. በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም (ለኹለት ዓመት)
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በተማሩበትና በአደጉበት በእንጦጦ መንበረ ፀሓይ ማርያም መልአከ ፀሓይ ተብለው አስተዳዳሪነት ተሹመው ስለነበር ዘወትር መልአከ ፀሓይ ተብለው መጠራቱን ይወዱታል፡፡ ክቡርነታቸው ለአስተዳዳሪነት ለመጨረሻ ጊዜ የተሾሙትና አገልግሎታቸውን ያቆሙት ሊቀ ሊቃውንት ተብለው በተሠየሙበት በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ነበር፡፡በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከ፲፱፻፺ ዓ.ም. ፳፻፬ ዓ.ም. በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህርነት ተመድበው ለዐሥራ ዐራት ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነትና በትጋት መጻሕፍተ ሐዲሳትን በማስተማር በርካታ ደቀመዛሙርትን አፍርተዋል፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ለማስተማር የነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ በመኾኑ ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ለሚያገለግሉ አንድ አባት በራሳቸው ወጪ እየተመላለሱ መጻሕፍተ ሐዲሳትን ያስቀጽሉ ነበር፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቆይታቸው ለደቀ መዛሙርቱ ለማስተማሪያነት የሚያገለግሉ ሦስት መጻሕፍትን፡
፩.የመጻሕፍተ ሐዲሳት አጠቃላይ ይዘትና ዋና ፍሬ ሐሳቦች
፪.በመጻሕፍተ ሐዲሳትለሚገኙ ምሳሌዎች፣ ታሪኮችና ተጨማሪ ማብራሪያ ለሚሹ ጉዳዮች መዝገበ ቃላት
፫. በመጻሕፍተ ብሉያትና ሐዲሳት መካከል ያለው አንድነትና ቁርኝት(ከወንጌለ ማቴዎስ እስከ ራዕየ ዮሐንስ
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ለማስፋፋት በነበራቸው መንፈሳዊ ቅንዓት፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ለማስፋፋት በነበራቸው መንፈሳዊ ቅንዓት፡
፩.የዓመቱን የሃምሳ ኹለቱን ሰናብት ምስባክናወንጌል አዘጋጅተው በመስበክ
፪. የውዳሴና ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜን፣
፫. ባሕረ ሐሳብንና አእማደ ምስጢርን፣
፬. ፍትሐ ነገሥትን በመቅረፀ ድምፅ ክር አስቀርጸዋል፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ከ፳፻፬ ዓ.ም. ጀምሮ በየዕለቱ ወደ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መመላለሱ እየደከማቸው ሲመጣ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ቤታቸው ኾነው የተለያየ የነገረ መለኮት ጥያቄ ይዘው ለሚመጡ እያስተማሩ ቆይተዋል፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ዕረፍት የሚባል ነገር ፈጽሞ አያውቁም፣ ዘወትር ያነባሉ፣ ዘወትር ይጽፋሉ፡፡ ዕረፍት ሲሹ በመኖሪያ ቤታቸው የሚያለሙትን የተለያዩ የጓሮ አትክልት ያርማሉ፣ ይኮተኩታሉ፡፡ በቤታቸው የተለያዩ የብራናና የወረቀት መጻሕፍትን አሰባስበዋል፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ የቅርብ ወዳጆቻቸውና አብሮ አደግ ጓደኞቻቸው መጻሕፍቶቻቸው ናቸው፡፡ ለመጻፍቶቻቸው ያላቸው ፍቅር ከፍተኛ ነው፡፡ ከመጻፍቶቻቸው ጋር ባላቸው ቅርብ ቁርኝት የተነሣ ለጠያቂዎቻቸው መልስ ለመስጠት ሲሹ የመጻሕፍቱን ሐሳባቸውን ብቻ ሳይኾን ሐሳቡ የሚገኝበት ገጽ ሳይቀር በቃላቸው ያስታውሳሉ፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡት ትንታኔ፣ የቃላት አጠቃቀማቸው፣ የምክንያት አደራረዳቸው በጣም የሚያስደንቅ ነው፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ አስተሳሰባቸው ድንቅና ምጡቅ፣ትምህርታቸው ጥልቅና ረቂቅ፣ ጨዋታቸው ጣፋጭና ቁጥብ፣ ንግግራቸው ቀጥተኛና ግልጽ ነው፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ባፍ በመጣፍ ወንጌልን የሰበኩ፣ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ቤተ ክርስቲያናቸውን የወከሉ፣ በቅዱስ ዮሐንስ፣ በልደትና በትንሣኤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚስተላልፉትን ቃለ ምዕዳን ሲያዘጋጁ የነበሩ የቀለም ቀንድ፣ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ፣ አስተዳዳሪ፣ መተርጕምና ተጠያቂ አባት ነበሩ፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ተርእዮን ፈጽሞ የሚሸሹ፣ በአለባበሳቸው ደምቀው መታየት የማይሹ፣ ፍቅረ ንዋይን የሚጸየፉ፣ ትኁትና ተሐራሚ የመጻሕፍተ ሐዲሳት፣ የመጻሕፍተ ሊቃውንትና የአቡሻኽር መምህር ነበሩ፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ለቅዱሳት መጻሕፍት ያላቸው ፍቅር እጅግ ታላቅ በመኾኑ ዘወትር ዕረፍት የላቸውም፡፡ የአረጋዊነት ዘመናቸውን ያሳለፉት በመኝታ ሳይኾን በምርምር ነበር፡፡ ያለ ማቋረጥ ያነባሉ፣ ያለ ዕረፍት ይጽፋሉ፡፡ ከንባብ ሲያርፉ ይጽፋሉ፡፡ ከጽሕፈት ሲያርፉ ደግሞ ያነበቡትን መጻሕፍት ምሥጢር ያራቅቃሉ፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ዘመን ጀምሮ ለመዓርገ ጵጵስና እየተጠየቁ እየሸሹ የኖሩ ታላቅ መንፈሳዊ አባት ነበሩ፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት ያላቸው ቀናኢነት ከፍተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ በነበሩበት ዘመናት በየሳምቱ እሑድ ከጸሎተ ቅዳሴ በኋላ በዓውደ ምሕረት ላይ ሕዝቡን አስተምረው ካሰናበቱ በኋላ እንደገና ወደ ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ገብተው ለአባላቱ ትምህርት ይሰጣሉ፡፡ ያን ዘመን የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት መርሐ ግብር ይከናወን የነበረው በማጥመቂያ ቤት ነበር፡፡ ይኽ ማጥመቂያ ቤት ለሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት አገልግሎት የሚሰጠው ከእርሳቸው አስቀድመው በነበሩት በገዳሙ አስተዳደሪ መልካም ፈቃድ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ አዳራሹ በየምክንያቱ እየተዘጋብን መርሐ ግብራችንን የምናካሂደው በመጠለያ ነበር፡፡ የማጥመቂያ ቤቱ አዳራሽ ትንሽ በመኾኑ ብዙ አባላት በሚመጡበት ወቅት መቀመጫ ቦታ ስለማይኖር ሕጻናት የምንማረው መሬት ላይ ተቀምጠን ነበር፡፡ ይኽንን ችግር ያስተዋሉት ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ የሰንበት ትምህርት ቤቱን አገልግሎት ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ሙሉ በሙሉ በታደሰበት ዘመን በመፈራረስ ላይ የነበረውን የአጼ ምኒልክን የግብር አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ኹኔታ አሳድሰዋል፡፡ አዳራሹን በአዳዲስ ወንበሮች ሞልተው የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በተመቻቸ ኹኔታ እንዲማሩ ምቹ ኹኔታዎችን ፈጥረዋል፡፡ በዚኽም ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ለዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ታላቅ ባለውለታ ናቸው፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ለሰንበት ትምህርት ቤት የነበራቸው ፍቅር ከፍተኛ በመኾኑ በሕይወተ ሥጋ ሳሉ አሁን ሥጋቸው ባረፈበት በደብረ ዘይት ከተማ ለሚገኘው ቃጂማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ከሁለት መቶ በላይ መጻሕፍቶቻቸውን በስጦታ አበርክተዋል፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እጅግ ቅርብ ናቸው፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝን በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እንዲኹም በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ሊቀ ሊቃውንት ተብለው ሲያስተዳድሩ አውቃቸዋለሁ፣ በአገልግሎታቸውም ሁለገብ ነበሩ፡፡ በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል በነበሩበት ጊዜ በዓቢይ ጾም ከመዘምራን ጋር ዳዊት ያስተዛዝሉ፣ ቀን ያስቀድሱ፣ በዘወትር ቀናት በተለይም በየወሩ በበዓለ ማርያም እንደሰሞነኛ ቀድሰው ያቈርቡ፣ በየሰንበቱ በዓውደ ምሕረት ይሰብኩ፣ በጾመ ማርያም ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ይተረጕሙ ነበር፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም አስተዳዳሪ በነበሩበት ዘመንም በጾመ ማርያም በደብረ መንክራት ኪዳነ ምሕረት ከማኅበረ ካህናቱ ጋር ጸሎተ ሰአታት ሲያደርሱ አድረው፣ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ አሰምተው፣ ያስቀድሱ ነበር፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ አእምሯቸው እጅግ ፈጣን ነው፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝን ከስድስት ዓመታት በፊት በመልአከ ምሕረት ቀሲስ ኃይለ ገብርኤል ይትባረክ አማካኝነት አግኝቼያቸው ነበር፡፡ በአንድ ወቅት የተለያዩ ጥያቄዎችን ይዤ ወደ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ መኖሪያ ቤት ሄጄ ነበር፡፡ በዕለቱ ከመኖሪያ ቤታቸው የደረስኩት ከጠዋቱ ፫ ፡ ፴ ነበር፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በፈገግታ ተቀብለውኝ ጥያቄዬን ያደምጡኝ ዠመር፡፡ ከዚያም ወደ መኝታ ቤታቸው በመሄድ ሦስት የብራና መጻሕፍትን ይዘው መጥተው ካጠገቤ ተቀመጡ፡፡ መጻሕፍቱን በጥያቄዬ መሠረት ለይተው ካስቀመጡ በኋላ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ምላሽ ከሰጡኝ በኋላ ዝርዝር ነገር ከፈለግኽ መጻሕፍቱን ተመልከት፡፡ በማለት ለጥያቄዎቹ ማብራሪያ የማገኝባቸውን ገጾች በቃላቸው ነገሩኝ፡፡ ከዚያም አንድ ጥያቄ ለመመለስ አቡሻኽር የሚባለውን የብራና መጽሐፍ አውጥተው በተለያየ ሐሳበ ዘመን(በሐሳበ ሳቤላ፣ በሐሳበ ዕብውራውያን፣ በሐሳበ ጽርእ፣ በሐሳበ ሶርያ፣ በሐሳበ አርመን) እያሰሉ ትክክለኛውን ጊዜ እያሳዩኝ ጀመር፡፡ በመካከል በሐሳበ ሳቤላ የመጣው ዘመንና ዕለት ከሌሎቹ ጋር ሳይገጥም ይቀራል፡፡ በእኔ በኩል ለጥያቄዬ በቂ ምላሽ አግኝቼ ስለነበር ስለ ልዩነቱ አልተጨነቅኩኝም፡፡ ስለዚኽም ወደ ሌላው ጥያቄ ተሸጋገርኩ፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ሌሎቹን ጥያቄዎች እየመለሱልኝ ቆይተን ምሳ ሰዓት ደርሶ ምሳ አብረን በላን፡፡ ቡና እየጠጣን አንዳንድ ነገሮች እያጫወቱኝ ቆየን፡፡ ከዚያም ወደ ቀደመው ጥያቄና መልሳችን ገባን፡፡ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ከቀኑ ፱ ፡ ፵፭ ላይ አኹን አገኘኹት በማለት ፊት ለፊት የተቀመጠውን አቡሻኽር አነሡት፡፡ ከዚያም ከዐራት ሰዓታት በፊት ከሌሎቹ አቆጣጠሮች ጋር አልግጥም ብሎ የነበረውን ሐሳባ ሳቤላ ተመልክተው ልዩነቱ ለምን እንደተፈጠረ በማሳየት ተመሳሳይ ዕለትና ዘመን አሳይተውኛል፡፡ ልብ አድርጉ እርሳቸው ለእኔ ሌሎች ጥያቄዎችን እየመለሱ፣ ሌሎች ነገሮችን እያጫወቱኝ፣ በአእእምሮአቸው ይኽንን ሐሳበ ሳቤላ ያመላልሱ ነበር፡፡ ይኽም ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ጉዳዮችን ማስታወስ የሚችል ባለፈጣን አዕምሮ ባለቤት እንደነበሩ ያሳያል፡፡
በሌላ ጊዜ ደግሞ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝን ለመጠየቅ ወደ መኖሪያ ቤታቸው አመራኹ፡፡ በዚኽ ዕለት አባታችን በእጃቸው የጻፏቸውን የብራና መጻሕፍት እንዲኹም ለደቀ መዛሙርቶቻቸው ያዘጋጁት ሦስት ረቂቅ መጻሕፍት አሳዩኝ፡፡ ረቂቅ መጻሕፍቱን ጊዜ ወስጄ አነበብኳቸው፡፡ ክቡር አባታችን በአረጋዊነት ዘመናቸው ድካም ሳያቸንፋቸው በትጋትና በእውቀት የጻፏቸው መጻሕፍት አቀራረባቸው፣ የቃላት አደራደራቸው፣ የዓረፍተ ነገር አወቃቀራቸው፣ የሐሳብ ፍሰታቸውና የዋቢ አጠቃቀሳቸው በጣም ያስደንቃል፡፡
ክቡር አባታችንን ትውልዱ ሃይማኖቱንና የሥነ ጽሑፍ ውበትን እንዲማርበት ለምን መጻሕፍቱን አታሳትሟቸውም? በማለት ጠይቅኳቸው፡፡ እርሳቸውም በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለማስተምራቸው ደቀ መዛሙርቴ ሰጥቼያቸው እነርሱ በየፊናቸው እየበጣጠሱ እያሳተሙት ነው፡፡ በማለት መለሱልኝ፡፡ እርሳቸው በደከሙበት ሌሎች ሲከብሩበት በመስማቴ በጣም አዘንኩ፡፡ ስለዚኽም መጻሕፍቱ የኅትመት ብርሃን እንዲያገኙ በማሰብ ምክረ ሐሳብ አዘጋጅቼ በቅርብ ለሚያውቋቸው ወንድሞች ሰጠኹ፡፡ ነገር ግን የበጎ ነገር ጠላት የተሻለ ነገር ያለ አስመስሎ ግን እንቅፋት የሚኾን ሐሳብ በማምጣት የድካማቸው ፍሬ ታትሞ እንዳይወጣ ጥረት አደረገ፣ ተሳካለትም፡፡ ይኸው ዛሬም የክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ለቤተ ክርስቲያን ልጆች የመድረስ ዕድሉ ዛሬም በጥያቄ ውስጥ ነው፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ወቅት በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሚያውቋቸው የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በሕይወተ ሥጋ በነበሩበት ጊዜ ታሪካቸው በምስል ወድምፅ ተዘጋጅቶ ለምእመናን እንዲደርስ በነበራቸው ጉጉት ቀረጻው ተጅምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይጠናቀቅ ቀርቷል፡፡ ይኽ ሥራ እንዲሠራ በመጓጓት በየዕለቱ እባካችሁ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በሞተ ሥጋ ሳይለዩን ሥራውን አጠናቁ፡፡ በማለት ያሳስቡን የነበሩት መልአከ ምሕረት ቀሲስ ኃይለ ገብርኤል ይትባረክ እንዲኹም የቀረጻ ሥራውን በማስጀመር ሲተጉ የነበሩት መልአከ ብርሃናት ቀሲስ ጌታቸው ደጀኔና የዓምደ ሃይማኖት ወንድማማቾች ማኅበር አባላት ነበሩ፡፡ ዛሬ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በሕይወተ ሥጋ ቢለዩንም ሥራቸው ሕያው ነውና የተጀመረውን የምስል ወድምፅ ዝግጅት አጠናቆ ለምእመናን ማድረሱ ብዙ የደከሙለት የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ወቅታዊ የቤት ሥራው ነው፡፡ ይኽንን የክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ የሕይወት ታሪክ የሚዘክረውን ሥራ ለፍጻሜ ለማድረስ ኹላችንም የመረባረብ ግዴታ አለብን፡፡
ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለሰባ ሦስት ዓመታት በትጋት፣ በፍቅር፣ በትህትና በታማኝነት ሲያገለግሉ ኖረው ጥቅምት ፳፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. በተወለዱ በ፹፫ ዓመታቸው ከዚኽ ዓለም በሕይወተ ሥጋ ተለይተው ሥርዐተ ቀብራቸው ደብረ ዘይት ከተማ በሚገኘው በቃጅማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡
የክቡር ሊቀ ሊቃውንት ታፈሰ ደስአለኝ በረከታቸው
ኦ እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ አቡነ ሣህለ ሥላሴ
|