ቅዱሳት
ኦ እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ አቡነ ወልደ አረጋዊ
አባ አሥራት መኩሪያ |
በደሴተ ጌቴሴማኒ አርባዕቱ እንስሳ ቤተ ክርስቲያን
ለአርባ ዓመታት ያገለገልሉ የነበሩት አባ አሥራት መኩሪያ ኅዳር ፳ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. አረፉ፡፡
በዛይ ሐይቅ ከሚገኙት ደስያት አንዱ ደሴተ ጌቴሴማኒ ነው፡፡
በደሴተ ጌቴሴማኒ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን የሥሉስ ቅዱስ አብ፣ ወልድ መንፈስ ቅዱስን መንበር የሚሸከሙ የኪሩቤል ወይንም
የአርባዕቱ እንስሳ መታሰቢያ ይገኛል፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ደብረ አብርሃም ለዘመናት ተዘግቶ ነበ፡፡ የደሴቱ ምእመናን ለረጅም ዘመናት መንፈሳዊ አገልግሎት አልነበራቸውም፡፡ የጥንቱ ቤተ ክርስቲያን በጨፈቃና
በጭቃ የተሠራ ነበር፡፡
ዛሬ የሚታየው ቤተ ክርስቲያን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ቢሠራም
የሚያስተምር፣ የሚያጠምቅ፣ ቀድሶ የሚያቆርብ፣ ሕዝቡን የሚያጽናና እንዲሁም ጸሎተ ፍትሐት የሚያደርስ ካህን አልነበረም፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ከፍቶ የሚያገለግል ካህን በማስፈለጉ ፲፱፻፷ ዎቹ ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ሉቃስ ካልዕ አባ አሥራት መኵያሪን ወደ ደሴተ ጌቴሴማኒ አመጧቸው፡፡
አባ
አሥራት መኩሪያ ወደ ዛይ ደስያት የመጡት ዲያቆን በነበሩበት ጊዜ ሲሆን በደብረ ጽዮን ደሴት ተምረው መንኵሰው ማዕረገ
ቅስና ተቀብለዋል፡፡ አባ አሥራት በደሴተ ጌቴሴማኒ አርባዕቱ እንስሳ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ለአርባ ዓመታት ያህል አገልግለዋል፣ ወደ ደሴተ ጌቴሴማኒ ከገቡ በኋላ ከደሴቱ ፈጽሞ አልወጡም፡፡
አባ አሥራት በዐርባ ዓመታት ቆይታቸው ዲያቆናት
አፍርተዋል፡፡ ሕይወታቸው የአባ አሥራት
መኵሪያ ሕይወት አጽንኦ በአትን ያስተምራል፡፡
አባ አሥራት ለሕዝቡ በሰንበትና
በበዓላት ኪዳን ያደርሱ ነበር፡፡ ቅዳሴ የሚቀደሰው እንደተገኘ ነው፡፡ ልዑካን ከተሟሉ ይቀደሳል፣ ካልተሟሉ ይታጎላል፡፡
በደሴተ ጌቴሴማኒ አርባዕቱ እንስሳ ቤተ ክርስቲያን ለአርባ ዓመታት ያገለገልሉ የነበሩት አባ አሥራት መኩሪያ ኅዳር
፳ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. አረፉ፡፡ ዛሬ የደሴቱን ነዋሪዎች የሚያስጨንቃቸው ያ ክፉ ዘመን ተመልሶ እንዳይመጣ ነው፡፡ የጌቴሴማኒ ምእመናን የነገ ዕጣ ፈንታቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ሲታሰብ
ያስጨንቃል፡፡ የአባታችን ጸሎታቸውና በረከታቸው በኹላችን ላይ ይደር፡፡
ኦ እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ አቡነ ወልደ አረጋዊ
No comments:
Post a Comment