የዛይ ስያሜ
በደስያቱ ላይ የሚኖረው የዛይ ሕዝብም ራሱን ዛይ በማለት የሚጠራበት ዘይቤያዊ ትርጓሜ አለው፡፡ ሕዝቡ ምድሪቱን ‹‹የዛይ ምድር›› ይላታል፡፡ በደሴቱ ያሉትን ነዋሪዎች ደብረ ዛይ ሲላቸው ከደሴቱ በአፍአ ያሉትን ደግሞ ደርገ ዛይ ይላቸዋል፡፡ ሕዝቡ ዛይ የሚለው ቃል ትርጓሜው ምንድን ነው? ሲባል ስመ አምላክ ነው ይላል፡፡ መነሻው እንዲህ ነው፡፡ ካህናተ አኵሱም ታቦተ ጽዮንን ይዘው በሰላም ወደ ደስያቱ በመድረሳቸው ሲደርሱ በመዝሙረ ዳዊት 0%8 ላይ ዛይ ብሂል ዝኩር እግዚአብሔር -ዘወትር የሚወሳ፣ የሚታሰብ እግዘአብሔር ማለት ነው፡፡ የሚለውን ዝማሬ በመያዝ ምድሪቱን ዛይ እንዳሏት ይነገራል፡፡ ይኸም ሕዝቡ ከመከራ የሠወራቸውን እግዚአብሔርን ዘወትር የሚያመሰግኑ በመሆናቸውና በደስያቱ ላይ እግዚአብሔርን ማመስገኛ አብያተ መቃድስ መሥራታቸውን ለማሳየት የተጠቀሙበት ሊኾን ይችላል፡፡
በዛይ ትውፊት አንድ ሰው ፍጹም አልዋሸሁም ሲል እኔ ዛይ ነኝ፡፡ ይላል፡፡ ስለዚህም ሕዝቡ ዛይ የሚለውን ስያሜ እንደ ስመ መሐላም ይጠቀምበታል፡፡
ስለ ደስያቱና ስለ ከተማው የጋራ ስያሜ በመነሻነት የቀረበው አስተያየት እርስ በእርሱ አይጣላምን? ቢሉ አይጣላም፡፡ ምክንያቱም አንዱ የአካባቢውን ሙቀት ለመግለጽ ‹‹ዝ-ዋዕይ›› ብሏል፡፡ ሁለተኛው በመልክአ ምድሩ ውበት ልቡ ሲነካ ዝ-ዋይ! ቢል፣ ሌላኛው ደግሞ የአካባቢውን ውሃማነት ለማሳየት ዝ-ማይ ቢል ሁሉም ይሆናል፡፡ ዝዋይ- ዋዕይነትን ከውበት፣ ውበትን ከማይነት አስተባብራ የያዘች ማራኪ ሥፍራ በመኾኗ በሁሉም ትውፊት የቀረቡት አስተያየቶች ሙሉ በሙሉ ሊያስኬዱ ይችላሉ፡፡ ዝዋይንም በሚገባ ይገልጻሉ፡፡
እና በዚህ ንባብ መሰረት "ዛይ" የህዝቡ ስም "ዝዋይ" የአገሩ ስም ነው ብለን መደምደም እንችላልን? ባልሳሳት እኔ የገባኝ በዚህ መልኩ ነው።
ReplyDeleteአሁን ባለው ሁኔታ ከተማው ባቱ ሲባል ሕዝቡ ዛይ በመባል ይጠራል፡፡ እኔ ግን ማንሣት የፈለግኩት ጥንተ ታሪኩን ነው፡፡ ወደፊት ራሱን ችሎ ለማየት እንሞክራለን፡፡
ReplyDelete